ለመስከረም 20 ምርጫ የተወዳዳሪዎች ቅስቀሳ መጀመር

ጳጉሜ 03/2013 (ዋልታ) መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም በሚካሄደው ምርጫ የሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የግል እጩ ተወዳዳሪዎች ከዛሬ ጳጉሜ 3 ጀምሮ የምረጡኝ ቅስቀሳ ማካሄድ እንደሚጀምሩ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡

ቦርዱ በምርጫ ጊዜ ሰሌዳው መሰረት ምርጫ ባልተካሄደባቸው አካባቢዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻ መስከረም 15 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅም ባወጣው መረጃ አመልክቷል፡