ከ3 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የተለያዩ ድጋፎች መደረግ

ጳጉሜ 03/2013 (ዋልታ) የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከ3 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ማህበረሰብ ክፍሎች የተለያዩ ድጋፎችን አደረገ፡፡

ክፍለ ከተማው የመልካምነትን ቀን ምክንያት በማድረግ ግምቱ ከ20 ሚሊየን ብር በላይ የሆነ የማዕድ ማጋራት መርኃግብር አድርጓል፡፡

ከ3 ሺህ 300 በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች የአዲሱ ዓመት መዋያ የስጦታ መርኃግብርም አካሂዷል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርኃግብር የታደሱ እና የተገነቡ 118 ቤቶችን ያስረከበ ሲሆን፣ በሶስተኛ ወገን የተያዙ ከ100 በላይ የሚሆኑ ቤቶችን ለአቅመ ደካሞች አስረክቧል፡፡

በሚልኪያስ አዱኛ