ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከሩዋንዳ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንና የሩዋንዳ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ቪንሰንት ቢሩታ

ነሐሴ 5/2015 (አዲስ ዋልታ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሩዋንዳ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ቪንሰንት ቢሩታን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በውይይታቸው በሁለቱ አገራት መካከል ስላለው የሁለትዮሽና የባለ ብዙ ወገን ግንኙነት በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስትር ቪንሰንት ቢሩታ ቀደም ሲል ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር መወያየታቸው ይታወቃል።