ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጅግጅጋ ገቡ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን

የካቲት 23/2014 (ዋልታ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ የልዑካን ቡድን ዛሬ ማለዳ ጅግጅጋ ገባ።

ልዑኩን የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢብራሒም ኡስማን እና የክልሉ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በጅግጅጋ ገራድ ዊልዋል አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አድርገውለታል።

የልዑካን ቡድኑ አባላት ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጋር በድርቁ አሁናዊ ሁኔታ ላይ ይወያያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከሶማሌ ብዙኃን መገናኛ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።