ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ከሆኑት ሬሚ ማሬሾ ጋር ተወያዩ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ከሆኑት ሬሚ ማሬሾ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ውይይቱ በአዲስ አበባ በፈረንሳይ ተቋራጮች የሚሰሩ ሜጋ ፕሮጀክችቶች አፈጻጸምን የተመለከተ እንደነበር ታውቋል፡፡

በተጨማሪም በሁለቱ አገራት መካከል የቆየውን የሁለትዮሽ ትብብር እና ወዳጅነት አጠናክሮ መቀጠል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ፍሬያማ ውይይት መደረጉን ከምክትል ከንቲባዋ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለከታል፡፡