የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአንጋፋ አትሌቶች የገንዘብ ስጦታ ተበረከተ

የአንጋፋ አትሌቶች ማህበር የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአንድ መቶ አንጋፋ አትሌቶች የ300 ሺህ ብር ስጦታ ዛሬ አበርክቷል፡፡

ለአንጋፋ አትሌቶቹ ለእያንዳንዳቸው የ3 ሺህ ብር የገንዘብ ስጦታውን የአንጋፋ አትሌቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ኮማንደር ጌጤ ዋሚ አበርክተዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የኢትዮጵያ አትሌትክስ ፌዴሬሽን ተወካይ አቶ አሰፋ በቀለና የአዲስ አበባ አትሌትክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ቢኒያም ምሩፅ የተገኙ ሲሆን፣ ይህ ድጋፍ በቀጣይ በቋሚነት እንዲቀጥል እየሰራን ነው ብለዋል።

ኮማንደር ጌጤ በዚሁ ወቅት እንዲህ ዓይነቱ የመደጋገፍ ባህል ወደፊትም መለመድ እንዳለበት መናገራቸውን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ አመልክቷል፡፡