ርዋንዳን 4 ለ 0 ያሸነፈችው ኢትዮጵያ

መስከረም 14/2014 (ዋልታ) በፊፋ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ የኢትየዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የርዋንዳ አቻውን 4 ለ 0 አሸነፈ፡፡
ረድኤት አስረሳኸኝ 2 ጎሎችን ስታስቆጥር አረጋሽ ካልሳ እና ቱሪስት ለማ ቀሪዎቹን ግቦች በስማቸው አስመዝግበዋል።
የ2022 የፊፋ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች የዓለም ዋንጫ በኮስታሪካ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ አስታውሷል፡፡