ሰርተን ራሳችንን መመገብ ካልቻልን ስንዴ እየለመንን ነጻነት የለም – ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

ግንቦት 27/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ሰርተን ራሳችንን መመገብ ካልቻልን ስንዴ እየለመንን ነጻነት የሚባል የለም ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንዳመላከተው ስንዴን ከመለመን ነጻ መውጣት የሚያስችል ብቁ የሆነ መልከአምድር አለን ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ይሄን የመሰለ መልከአምድር ይዛ፣ ውሃ ይዛ መንግስት እና ህዝብ በተለይም አርሶአደሩ በትክክል የግብርናን ምርት እና ምርታማነትን ማሳደግ ጉዳይ ከሀገር ህልውና ጉዳይ ጋር የተያያዘ መሆኑን አውቆ ሰርተን ራሳችንን መመገብ ካልቻልን ስንዴ እየለመንን ነጻነት የሚባል ነገር የለም ብለዋል።