በማዕድን ምርመራ፣ ምርትና ኤክስፖርት ፈቃድ የወሰዱ 972 ድርጅቶች ፈቃዳቸው ተሰረዘ

ሰኔ 15/2014 (ዋልታ) በማዕድን ምርመራ፣ ምርትና ኤክስፖርት ዙሪያ ፈቃድ ወስደው የነበሩ 972 ድርጅቶች ፈቃዳቸው መሰረዙን የማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ።

የማዕድን ሚኒስትር ታከለ ኡማ በሰጡት መግለጫ የተለያዩ የማዕድን ኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው በገቡት የውል ስምምነትና ባፀደቁት የሥራ ፕሮግራም መሰረት ሥራቸውን ያላከናወኑ 972 ድርጅቶች ፈቃዳቸው እንዲሰረዝ መደረጉን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ባለፉት አስራ አንድ ወራት ኢትዮጵያ ከወርቅ ምርት 513 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷንም አስታውቀዋል፡፡

ዘርፉ እየተገባደደ በሚገኝው የበጀት ዓመት ከቡና ቀጥሎ ሁለተኛው የውጪ ምንዛሬ ማስገኘቱንም ጠቁመዋል።

በህይወት አክሊሉ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW