በሪጋ የጎዳና ላይ ሩጫ ለተሳተፉ አትሌቶች የሽልማት መርኃ ግብር ተካሄደ

መስከረም 22/2016 (አዲስ ዋልታ) በላቲቪያ ሪጋ የዓለም የጎዳና ላይ ውድድር ለተሳተፉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን አባላት የእውቅና እና ሽልማት መርኃ ግብር ተካሂዷል፡፡

በሪጋ የዓለም የጎዳና ላይ ውድድር የተሳተፉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን አባላት ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ መግባታቸውም ተመላክቷል፡፡

ልዑካኑ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት እና የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረ/ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ አቀባበል ማድረጋቸውን የአቲሌትክስ ፌዴሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

በበመቀጠልም በላቲቪያ ሪጋ በተካሄደው የዓለም የጎዳና ላይ ውድድር ለተሳተፉ አትሌቶች በስካይ ላይት ሆቴል የእውቅና እና ሽልማት መርኃ ግብር ተካሂዷል፡፡

ኢትዮጵያ በሪጋ የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ሁለት ወርቅ፣ አራት ብር እና አንድ የነሐስ ሜዳልያ በማግኘት 2ኛ ደረጃ በመያዝ ማጠናቀቋ ይታወሳል፡፡