በርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የተመራ ልዑክ በገላን ከተማ የልማት ፕሮጀክቶችን እየጎበኘ ነው

ጥር 28/2014 (ዋልታ) በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የተመራ ልዑክ በገላን ከተማ እየተሰሩ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶችን እየጎበኘ ነው።

ልዑኩ በአርሶ አደር ኢንቨስት የተደረገውን የብሎኬት ማምረቻ ጎብኝቷል።

የብሎኬት ማምረቻው ከስምንት ወራት በፊት መጀመሩ የተገለፀ ሲሆን 40 ለሚሆኑ ሥራ አጦች የሥራ እድል መፍጠሩ ተነግሯል።

በጉብኝቱ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድርን ጨምሮ የክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አዎሎ አብዲ እና በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የኦሮሚያ ከተማ ልማት አስተባባሪ አዲሱ አረጋ  ተሳትፈውበታል።