በአማራና አፋር ክልሎች የወደሙ የጤና ተቋማትን መልሶ ለመገንባት ከ36 ቢሊየን ብር በላይ ያስፈልጋል ተባለ

ጥር 28/2014 (ዋልታ) በአማራ እና አፋር ክልሎች የወደሙ የጤና ተቋማትን መልሶ ለመገንባት ከ36 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የሚጠይቅ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የተቋሙን የ6 ወራት የሥራ ክንውን ለኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል፡፡

በዚህም በአማራና አፋር ክልሎች 42 ሆስፒታሎች፣ 523 ጤና ጣቢያዎች፣ 2 ሺሕ 359 ጤና ኬላዎች በአሸባሪው ሕወሓት ዘረፋና ውድመት ደርሶባቸዋል ብለዋል።

አክለውም በአካባቢው ለማኅበረሰቡ ይሰጥ የነበረው የጤና አገልግሎት መስተጓጎሉን መግለጻቸውን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡