በኅዳር ወር ከ32.7 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ

የገቢዎች ሚኒስቴር

ታኅሣሥ 7/2015 (ዋልታ) የገቢዎች ሚኒስቴር በኅዳር ወር ብቻ 32 ቢሊዮን 785 ሚሊየን 760 ሺሕ ብር በመሰብሰብ ከዕቅድ በላይ አፈፃፀም ማስመዝገቡን አስታወቀ፡፡

በዚህም ለመሰብሰብ ካቀደው 30 ቢሊዮን 20 ሚሊየን 180 ሺሕ ብር ውስጥ 32 ቢሊዮን 785 ሚሊየን 760 ሺሕ ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 109.21 በመቶ ማሳካቱን ነው የገለጸው፡፡

አፈጻፀሙ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻፀር የብር 9 ቢሊዮን 380 ሚሊየን 130 ሺሕ እድገት እንዳለው ተመላክቷል፡፡

በተመሳሳይ ሚኒስቴሩ በ5 ወራት ውስጥ ሊሰበስብ ካቀደው 196 ቢሊየን 536 ሚሊየን 690 ሺሕ ብር ውስጥ 195 ቢሊየን 771 ሚሊየን 570 ሺሕ ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 99.61 በመቶ ማሳካት መቻሉን አስታውቋል፡፡

አፈፃፀሙ ካሳለፍነው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ48 ቢሊየን 403 ሚሊየን 270 ሺ ብር ብልጫ ያሳየ ሲሆን ይህም የ32.85 በመቶ እድገት እንዳለው ተጠቁሟል፡፡

በቀሪዎቹ ወራት በ2015 በጀት ዓመት የተያዘውን እቅድ በማሳካት ከዕቅድ በላይ ገቢ ለመሰብሰብ እንደሚሰራ ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured