ከ1 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የአማራ ሕዝብ ሙዚየም ግንባታ ተጀመረ

የአማራ ሕዝብ ሙዚየም ግንባታ

ታኅሣሥ 7/2015 (ዋልታ) የአማራ ክልል መንግሥት ከ1 ቢሊየን 186 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የአማራን ሕዝብ ሙዚየም ማስገንባት መጀመሩን አስታወቀ፡፡

ሙዚየሙ የአማራን ሕዝብ ቅርስ፣ ታሪክና ባሕሉን ለማስቀመጥ ከማገልገል ባለፈ አንዱ የቱሪዝም መዳረሻ እንደሚሆን የታመነበት ሲሆን በአማራ ሕንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ይገነባል ነው የተባለው።

ሙዚየሙ የሚገነባው በባሕር ዳር ከተማ ሲሆን በአጠቃላይ በ15 ሺሕ 600 ካሬ ላይ እንደሚያርፍም ተገልጿል።

በሙዚየሙ የግንባታ ማስጀመሪያ መርኃግብር ላይ ከፍተኛ የክልሉ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን የአሚኮ ዘገባ አመላክቷል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured