በኤርትራውያን ስደተኞች ላይ የሽብርተኛው ቡድን እያደረሠ ያለውን ጥቃት የሚቃወም ሰልፍ ተካሄደ

ሐምሌ 22/2013(ዋልታ) – በኤርትራውያን ስደተኞች ላይ የህወሓት ፅንፈኛ ቡድን እያደረሠ ያለውን ጥቃት በመቃወም በአዲስ አበባ የሚገኙ ኤርትራውያን የተቃውሞ ሰልፍ እያካሄዱ ነው።

ኤርትራዊያኑ ስደተኞች በአዲስ አበባ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት መስሪያ ቤት ተገኝተው ነው ድምፃቸውን ያሰሙት።
ስደተኞቹ ከዚህ ቀደም በተለያየ ጊዜ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብና ለመንግስታቱ የስደተኞች ድርጅት በደብዳቤና በአካል በመገኘት መልዕክት ብናስተላለፍም ምላሽ አላገኘንም ብለዋል።
አለም አቀፍ ማህበረሰብ አሸባሪው ህወሓት በኤርትራውያን ስደተኞች ላይ የሚያደርሰውን ግፍ እና ግድያ ሊቃወም እና ሊያስቆም ይገባልም ነው ያሉት፡፡
በተቃውሞ ሰልፉ ላይ ህጻናት ስደተኞች የተገኙ ሲሆን «እኛ ስደተኞች እንጂ ወንጀለኞች አይደለንም» የሚሉ መፈክሮች በመያዝ የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰምተዋል።
(በሜሮን መስፍን)