የስነ ልክ መሳሪያዎችን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ በተደረገ የቁጥጥር ስራ ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ተገኘ

ሐምሌ 22/2013 (ዋልታ) – የስነ ልክ መሳሪያዎችን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ በተደረገ የቁጥጥር ስራ ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ተገኘ፡፡

ከውጪ ወደ ሀገር ውስጥ በገቡና ለልዩ ልዩ አገልግሎት የሚውሉ ህጋዊ የስነ ልክ መሳሪያዎችን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ በተደረገ የቁጥጥር ስራ 6 ሚሊየን 154 ሺህ 358 ብር ገቢ መገኘቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ገቢው የተገኝው በ2013 በጀት ዓመት ለ1 ሚሊየን 620 ሺህ 180 የመለኪያ መሳሪያዎችና ለ2 ሺህ 781 የፈሳሽ ማጓጓዣ ቦቴዎችን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ በተደረገ ቁጥጥርና ክትትል መሆኑን ከንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡