ሰኔ 12/2013 (ዋልታ) – በከፋ ዞን በመጪው ሰኞ ለሚደረገው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተጠናቀቁ መሆኑ ተገለፀ።
በአሁኑ ወቅት የምርጫ ቁሳቁስ በዞኑ የደረሱ ሲሆን፣ ወደየምርጫ ጣቢያዎቹ እየተከፋፈሉ ይገኛል።
በዞኑ ሰባት የምርጫ ክልሎች በ590 የምርጫ ጣቢያዎች ምርጫው የሚካሄድ ሲሆን፣ ሰባት የፖለቲካ ፓርቲዎች ለፌደራል እና ክልል ምክር ቤት ይፎካከራሉ ነው የተባለው።
በዞኑ ለዘንድሮው ሀገራዊ ምርጫ 524 ሺህ 686 ዜጎች ድምጽ ለመስጠት መመዝገባቸውን ተጠቁሟል።
(በአሳየናቸው ክፍሌ)