በደቡብ ክልል መስከረም 20 ስለሚካሄደው ምርጫ

መስከረም 5/2014 (ዋልታ) በደቡብ ክልል የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በክልሉ የፊታችን መስከረም 20 በሚካሄደው ምርጫ ዙሪያ እየተወያየ ነው፡፡
በውይይቱ በጸጥታ ምክንያት ምርጫ ያልተካሄደባቸው፣ በተለያዩ ምክንያቶች ምርጫ የሚደገምባቸውና በፍርድ ቤት ውሳኔ ምርጫ እንዲደገም የተወሰነባቸው 31 የምርጫ ክልሎች መኖራቸው ተመላክቷል፡፡
በዚሁ መሰረት ፓርቲዎቹ በእነዚህ የምርጫ ክልሎች ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በሚካሄድበት ሁኔታና በቅድመ ዝግጅቶች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
በክልሉ 21 ተፎካካሪ ፓርቲዎች ለ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ተመዝግበው እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ ወ/ሮ ጸሃይ ወራሳ እንደገለጹት የምክር ቤት አባል ፓርቲዎች በምርጫው ዙሪያ ሊያጋጥሙ በሚችሉ ችግሮች ዙሪያ ተወያይቶ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡