በዳውሮ ዞን የድምፅ አሰጣጥ ሂዴት

መስከረም 20/2014 (ዋልታ) በዳውሮ ዞን በሎማ ቦሳ የምርጫ ክልል የሚካሄደው 6ኛ ሀገራዊ ምርጫና በዞኑ በሁሉም አከባቢ የሚካሄደው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ህዝበ ውሳኔ የድምፅ አሰጣጥ ሂዴት በዞኑ በሁሉም አከባቢዎች በሰላም እየተካሄደ ነው።

የድምፅ አሰጣጥ ሂዴቱ ሰላማዊና የተረጋጋ መሆኑ እንዳስደሰታቸው ድምፃቸውን የሰጡ መራጮች ገልፀዋል።

በምርጫው ለመሳተፍ ከዞን ውጭ የሚኖሩ የአከባቢ ተወላጆችም ተገኝተው ድምፃቸውን በመስጠት ላይ እንደሚገኙ ከዞኑ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።