በገንዘብ ሚኒስትሩ የተመራ የፌደራል የድጋፍ እና ክትትል ቡድን በሃዋሳ ከተማ የልማት ስራዎችን ጎበኘ


መጋቢት 8/2016 (አዲስ ዋልታ) በገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ የተመራ የፌደራል የድጋፍ እና ክትትል ቡድን በሃዋሳ ከተማ አስተዳደር እየተከናወኑ በሚገኙ የልማት ስራዎች ላይ የመስክ ምልከታ አካሄደ።

ቡድኑ ላለፉት ቀናት የመንግስት እና የፓርቲ ተግባራት አፈፃፀም ላይ ከሲዳማ ክልል የስራ ኃላፊዎች ጋር መክሯል።

የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ መኩሪያ ማርሻዬ በከተማዋ የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት የከተማ ግብርና ስራ እንዲለመድ ማድረግን ጨምሮ አምራቹ እና ሸማቹን በቀጥታ የሚያገናኙ የግብይት ማዕከላትን በማቋቋም እየተሠራ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

የስራ ዕድል ፈጠራ፣ የመሠረተ ልማት ተደራሽነት እና ሌሎች ሰው ተኮር የበጎ ፍቃድ ስራዎች በከተማዋ በ2016 ግማሽ ዓመት ልዩ ትኩረት ተደርጎባቸው ከተመሩ ዘርፎች መካከል ስለመሆናቸው ተናግረዋል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ በበኩላቸው የመስክ ምልከታው በክልሎች የተያዙ የልማት እቅዶች ያሉበት ደረጃን በመለየት ጠንካራ ጎኖችን ለማጠናከር እና ክፍተቶችን ለማረም ያለመ መሆኑን አስረድተዋል።

በሃዋሳ ከተማ በሌማት ትሩፋት መስክ የተከናወኑ መልካም ተሞክሮዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም መናገራቸውን የኢቢሲ ዘገባ አመላክቷል።