በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣና ከ100 ሺሕ ለሚልቁ ዜጎች የስራ እድል ተፈጠረ


መጋቢት 8/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገንብቶ በሚያስተዳድራቸው 12 ኢንዱስትሪ ፓርኮችና የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣና ከ100 ሺሕ ለሚልቁ ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩ ተገለጸ።

የስራ እድሉ ከተፈጠረላቸው ዜጎች መካከል ከ75 በመቶ በላይ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውም ተገልጿል።

የስራ እድል ፈጠራው የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደ ሀገር እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት የሚታይ ውጤት እያመጡ መሆኑም ተመላክቷል።

ኮርፖሬሽኑ አሁንም ወደ ስራ የሚያስገባቸው ኢንቨስትመንቶች ሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ እንዲሆኑ እየሰራ እንደሚገኝ የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል።