ቦርዱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመራጮች ምዝገባ የሚያካሂዱበትን የመመዝገቢያ ሊንክ ይፋ አደረገ

ሚያዝያ 12/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመራጮች ምዝገባ የሚያካሂዱበትን የመመዝገቢያ ሊንክ ይፋ አድርጓል፡፡

ቦርዱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመራጮች ምዝገባን በተመለከተ በሰጠው መግለጫ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመራጮች ምዝገባ በኢንተርኔት እንደሚካሄድ ገልጿል፡፡

ከምርጫ ቦርድ የተገኘው መረጃ እንዳመላከተው ይህን ሂደት ለፖለቲካ ፓርቲዎች አቅርቦ ምክክር ተደርጎበታል፡፡

በዚህም መሰረት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ለሚቀጥሉት 15 ቀናት እስከ ሚያዝያ 26 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ ይችላሉ ነው የተባለው፡፡

(የመመዝገቢያ ሊንክ – http://www.nebe.org.et/ovrs መሆኑን ቦርዱ አስታውቋል።)