ተቋሙ ስያሜውን ከኤጀንሲ ወደ አስተዳደር መለወጡን ገለጸ

የካቲት 11/2014 (ዋልታ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ስያሜውን ከኤጀንሲ ወደ አስተዳደር መለወጡን አስታወቀ፡፡

ተቋሙ ቀደም ሲል የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ተብሎ ሲጠራ መቆየቱ ይታወቃል።

ሆኖም በመንግሥት አስፈፃሚ አካላት ሥልጣን እና ተግባራት መወሰኛ አዋጅ መሰረት “የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር” በሚል ስያሜ መለወጡን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡