ትምህርት ሚኒስቴር ከደቡብ ሱዳን የከፍተኛ ትምህርት፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራረመ

ኅዳር 21/2015 (ዋልታ) የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ከደቡብ ሱዳን የከፍተኛ ትምህርት፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።

የሁለቱ ሀገራት የትምህርት ሚኒስትሮች የተፈራረሙት ሰነድ በትምህርት ዙሪያ በጋራ ለመስራት እንደሚያስችላቸው ተጠቁሟል።

ስምምነቱ ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን የምትሰጠውን ነጻ የትምህርት እድል ለማሳደግ ያስችላል ያሉት የትምህርት ሚኒስትሩ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የትምህርት ዘርፍ የቆየ ትብብርና ወዳጅነት የበለጠ እንደሚያጠናክረውም ተናግረዋል።

የደቡብ ሱዳን የከፍተኛ ትምህርት፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ጋብርኤል ቻንግሰን ቻንግ በበኩላቸው ሰነዱ ሁለቱ አገራት በትምህርት መስክ ያላቸውን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያደርሰው ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት በሚሰጠው ነጻ የትምህርት እድል በርካታ ደቡብ ሱዳናውያን የነጻ ትምህርት ተጠቃሚ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW