የአለም የስራ ፈጠራ ሳምንት በአገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ ነው

ኅዳር 21/2015 (ዋልታ) የአለም የስራ ፈጠራ ሳምንት በአገር አቀፍ ደረጃ በስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር አዘጋጅነት በዛሬው እለት መከበር ጀምሯል፡፡

ከ200 በሚበልጡ የአለም አገራት ለ15ኛ እንዲሁም በአገራችን ለ9ኛ ጊዜ የስራ ፈጠራ ሳምንት የሚከበር ሲሆን፤ “ሚሊየን ፈተናዎች ሚሊየን እድሎች” በሚል መሪ ቃል የዘንድሮው የዓለም የስራ ፈጠራ ሳምንት ይካሄዳል ።

የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈርሃት ካሚል፤ አገራችን በርካታ የሰው ሀይል፣ አቅም እና ጥሬ ሀብት ያለት በመሆኑ ይህንን እድል ለችግሮቻችን መፍትሄ የሚሆኑ ስራዎችን ለመፍጠር እንጠቀምበታለን ብለዋል።

ሚሊየን ችግሮቻችንን ወደ ሚሊየን እድሎች ለውጠን አገራችን የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ በስራ ፈጠራ እናስቀጥላለን ያሉት ሚኒስትሯ የሚመለከታቸው ሁሉ ለስኬቱ በጋራ እንዲሰሩ ጠይቀዋል።

በሳምንቱ የተለያዮ ሲምፖዚየሞች፣ ስልጠናዎች እና የልምድ ልውውጦች ይካሄዳሉ ተብሏል።

በቁምነገር አሕመድ