ግንቦት 03/2021 (ዋልታ) – አሜሪካ በአገራት ላይ እያደረገች ያለው ስለላ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ቻይና ገለጸች፡፡
በዓለም ቁጥር አንድ የማዳመጥ ኃይል በመባል ዕውቅና የተሰጣት አሜሪካ የአጋር አገራት ሚስጥሮችን ለመስረቅ የተለያዩ መንገዶችን እየተጠቀመች መሆኑን የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢን ገልጸዋል፡፡
ቃልአቀባዩ 100 በሚጠጉ የአሜሪካ ኤምባሲዎች እና ቆንስላ ጽህፈት ቤቶች የሚስጥር ክትትል መሣሪያዎችን አቋቁማለችም ብለዋል፡፡
ከቀናት በፊት በመገናኛ ብዙኃን እንደተገለጸው የአሜሪካ የአውሮፓ አገራት አጋሮችን ውይይትን በድብቅ በመከታተል እና ከስልክ መስመር ጋር በማገናኘት የፈጸመችው ተግባር ግዙፉን ዓለም ዓቀፍ የሚስጥሮች ስርቆት ጫፍ መሆኑን ገልጸው፣ ለዚህም አሜሪካ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ማብራሪያ እንደምትሰጥ ተናግረዋል፡፡
የአሜሪካ ብሄራዊ ደህንነት ኤጀንሲ ከዴንማርክ የውጭ የስለላ ክፍል ጋር በመሆን ከ2012 እስከ 2014 በስዊድን ፣ በኖርዌይ ፣ በጀርመን እና በፈረንሣይ ባሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ላይ ስላላ ማካሄዷን በውጭ ሀገር የመገናኛ ብዙሃን ኤጄንሲዎች የተደረገው የጋራ ምርመራ አመላክቷል፡፡
ዋንግ አሜሪካን እያካሄደች ያለውን መጠነ ሰፊ የሆነ የአገራት ሚስጥሮች ስርቆት በአፋጣኝ እንድታቆም እና የሌላ አገር ኢንተርፕራይዞችን መጨቆኗን እንድታቆም ማሳሰባቸውን ሲጂቲኤን አስነብቧል፡፡