የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት አዲስ አበባ ገቡ

ግንቦት 26 / 2013 (ዋልታ) – የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት አኪንውሚ አዴሲና በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ይህንኑ አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ዶ/ር አኪንውሚ አዴሲናን “የአፍሪካ እውነተኛ ልጅ እና የኢትዮጵያ አጋር ወደ ኢትዮጵያ እንኳን ደኅና መጡ” ብለዋቸዋል፡፡