አሸባሪው ሕወሓት በወረራ በያዘቸው አካባቢዎች በሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ላይ ከፍተኛ ውድመት መድረሱ ተገለጸ

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል

ታኅሣሥ 7/2014 (ዋልታ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አሸባሪው ሕወሓት በወረራ በያዘቸው አካባቢዎች በሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ላይ ከፍተኛ ውድመት እንዳደረሰ በጥናት ማረጋገጡን አስታወቀ።

በደሴ፣ ኮምቦልቻ እና ሌሎችም አካባቢዎች በጥናቱ በተካተቱ 40 ኢንዱስትሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ሚኒስቴሩ በቦታው ተገኝቶ ባካሄደው ጥናት አረጋግጭያለው ብሏል።

በዚህም ከ40 ኢንዱስትሪዎች በ8 ቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰ ሲሆን እነዚህም ለኅብረተሠቡ ከፍተኛ ጠቀሜታ በሚሰጡ የውሃ መስመር እና ምግብ ነክ ምርቶች የሚያመሩቱ ፋብሪካዎች እንደሆኑና የተደራጀ ዘረፋ እና ውድመት እንደደረሰበት ተመልክቷል።

አሸባሪው ሕወሓት ለኢትዮጵያ ያለውን ጥላቻ ያሰየበትን ሀገር የማፍረስ ሥራ ሠርቷል ያሉት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ኢንዱስትሪዎቹ በፍጥነት ወደ ሥራ እንዲመለሱ እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል።

በትዝታ ወንድሙ