በደሴ ከተማ 82 ትምህርት ቤቶች በአሸባሪው ትሕነግ ውድመትና ዘረፋ ተፈፅሞባቸዋል

ታኅሣሥ 7/2014 (ዋልታ) በደሴ ከተማ የሚገኘው የሆጤ ሁለተኛ ደረጃና አጠቃላይ የመሰናዶ ትምህርት ቤት በአሸባሪው ትሕነግ የወራሪ ኃይል ውድመት እንደደረሰበት ተገለጸ።
የሽብር ቡድኑ ወራሪ ኃይል በትምህርት ቤቱ የላቦራቶሪ ቤተ ሙከራ ሙሉ ለሙሉ በእሳት እንዲወድም ህንፃውም ከጥቅም ውጭ እንዲሆንም አድርጓል።
አሸባሪ ቡድኑ የአማራ ተማሪዎች ከትምህርት እንዲገለሉና ከቴክኖሎጂ ጋር እንዳይገናኝ በማሰብ 251 ኮምፒውተርና 39 ፕላዝማ ከሆጤ አጠቃላይና ከፍተኛ ትምህርት መሰናዶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እንደዘረፈም ተነግሯል።
ከትምህርት ቤቱ 10 ሺሕ መፅሐፍ፣ 26 ፕሪንተርና 4 ፎቶ ኮፒ ማሽን በሽብር ቡድኑ ተወስዷል ነው የተባለው።
የሆጤ አጠቃላይና ከፍተኛ ትምህርት መሰናዶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ1951 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን በፈረቃ 10 ሺሕ ተማሪዎችን ያስተናግድ ነበር።
አሸባሪው ትሕነግ ደሴን ወርሮ በቆየበት በከተማዋ ከሚገኙ ከ100 በላይ ትምህርት ቤቶች 82 የሚሆኑትን ትምህርት ቤቶች በማደም የሚፈልገውን ዘሮፎ ወደ መቀሌ ወስዷል ነው የተባለው።
የ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ እንደይስተጓጎሉ በደሴ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተማሩ የቀድሞ ተማሪዎች የወሎ ተወላጆች መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
በምንይሉ ደስይበለው (ከግንባር)