አሸባሪው ሕወሓት ያደረሰውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት የሚያሳይ የፎቶ አውደ ርዕይ  ለእይታ ክፍት ሆነ

የፎቶ አውደ ርዕይ

ጥር 1/2014 (ዋልታ) አሸባሪው ሕወሓት በአማራ ክልል ያደረሰውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት የሚያሳይ የፎቶ አውደ ርዕይ በባሕር ዳር ከተማ ለሕዝብ እይታ ክፍት ሆነ።

የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ጀንበር (ዶ/ር) በፎቶ አውደ ርዕዩ መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ እንደገለጹት አሸባሪው ሕወሓት በክልሉ በርካታ ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት አድርሷል።

የውድመቱን መጠን ሙሉ በሙሉ በተከፈተው አውደ ርዕዩ ማሳየት እንደማይቻል የጠቆሙት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ከዘረፋና ከውድመት የተረፉ የጉዳት ቅሬቶች በአውድ ርዕዩ  ላይ መቅረባቸውን አመልክተዋል።

በቀጣይ መሰል ችግሮችን ለመከላከል ከፋፋይ አጀንዳዎችን ወደ ጎን በመተው በአንድነት ጠንካራ ሆኖ መገኘት እንደሚገባም ተናግረዋል።

ታሪካዊ የሆነውን የፎቶ አውደ ርዕይ ኅብረተሰቡ በአካል በመገኘት መጎብኘት እንዳለበት  ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ አሳስበዋል።

በአውደ ርዕዩ መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና የዲያስፖራ አባላት መገኘታቸው ኢዜአ ዘግቧል።