የመከላከያ ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በተገኙበት እየተመረቀ ነው

ጥር 1/2014 (ዋልታ) ጦር ኃይሎች አሮጌው አውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ የሚገኘውና በግዙፍነቱም ሆነ በኪነ-ህንፃ ውበቱ እጅግ ዘመናዊ እንደሆነ የተነገረለት የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት እየተመረቀ ይገኛል።
በ13 ሺሕ ካሬ ላይ ያረፈው ባለ 5 ወለል ህንፃ ከ700 በላይ ቢሮዎች ያሉት ሲሆን የተለያየ ደረጃ ያላቸው የስብሰባ አዳራሾች፣ ቤተመጽሐፍት፣ የምርምር ማዕከላትና የተደራጀ የመረጃ ማዕከል በውስጡ አካቷል፡፡
ከዘጠኝ ዓመት በፊት ግንባታው የተጀመረው ዋና መስሪያ ቤቱ ሄሊኮፕተርና መጠነኛ የጦር ጄቶቸን ማሳረፍ የሚችል 36 ሺሕ ካሬ ቦታም እንዳለው ተመላክቷል።