ኢትዮጵያዊያን ለኢትዮጵያዊያን በሚል መሪ ሀሳብ አመታዊ ነፃ የህክምና አገልግሎት መስጠት ተጀመረ

ነሃሴ 9/2013(ዋልታ) – ኢትዮጵያዊያን ለኢትዮጵያዊያን በሚል መሪ ሀሳብ አመታዊ ነፃ የህክምና አገልግሎት መስጠት ተጀምሯል፡፡

የበጎ ፍቃድ አገልግሎትን አጠናክሮ ለመቀጠልና  ማህበራዊ ሃላፊነትን ለመወጣት የሚያስችል ስራዎች እያከናወነ መሆኑን  የዶክተር እመቤት የጥርስ ህክምና ማዕከል አስታውቋል።

ማዕከሉ ገንዘብ ከፍለው መታከም ለማይችሉና በጥርስ ህመም ችግር ለሚሰቃዩ ከ 500 በላይ  ዜጎች ነፃ  ህክምና እሰጣለው ብሏል።

ማህበራዊ ሃላፊነትን ከመወጣት አንፃር በቀጣይም የሚሰጠውን አገልግሎት አጠናክሮ እንደሚቀጥል የተቋሙ መስራችና ባለቤት ዶ/ር እመቤት ገዛኸኝ ተናግረዋል።

በመድረኩ የተገኙት የጤና ሚኒስቴር ተወካይ ዶ/ር ጳውሎስ ማርቆስ በአለም ጤና ድርጅት መስፈርት መሰረት ከ71 ፐርሰንት በላይ ህክምና የሚሰጠው  ከአንገት በላይ ለሆኑ ህክምና ነው ያሉ ሲሆን በተለይም በሀገራችን በብዛት የጥርስ ህክምና የሚሰጡት የግል ክሊኒኮች ናቸው ይህንን ወደተለያዩ መንግስታዊ ሆስፒታሎች  ለማስፋት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

(በሱራፌል መንግስቴ)