ኢትዮጵያዊ ቤተሰብ ከትምህርት ጋር ያለውን ቁርኝት የሚያሳየው ፎቶ የዓመቱ የምድር ፎቶ አሸናፊ ሆነ


ነሀሴ 4/2013 (ዋልታ) –
አንድ ኢትዮጵያዊ ቤተሰብ ከትምህርት ጋር ያለውን ቁርኝት የሚያሳየው ፎቶ የ2021 የምድር ፎቶ ውድድር አሸናፊ መሆኑ ተገለጸ።
በየአመቱ የሚካሄደው የምድር ፎቶ ውድድር የ2021 አሸናፊዎች ይፋ ሆነዋል።
ሮዚ ሃላም ያነሳችው የኢትዮጵያን የአንድ ቤተሰብ የትምህርት ሂደት የሚያሳየው ትይዩ ፎቶ አሸናፊ መሆኑ ተገልጿል።
ሮዝ ሃላም በደቡብ ኢትዮጵያ ያነሳችው ፎቶዎች የሰላማው ማረቆ የተባለች ታዳጊ የትምህርት ሂደትን የሚያሳይ ሲሆን ተዳጊዋ ከቤተሰቧ ለትምህረት ገበታ የበቃች ልጅ መሆኗን ያመለክታል።
የታዳጊዋ ቤተሰቦች በቤተሰብ ትምህርት ውስጥ የታቀፉ መሆናቸውም በፎቶው ህዳግ ላይ ሰፍሯል።
የታዳጊዋን የትምህርት ሂደትና የቤሰቦቿን ሁኔታ የሚያሳየው ትይዩ ፎቶ የምድር ፎቶ የሰዎች ዘርፍ አሸናፊ መሆኑ ይፋ ተደርጓል።
ከዚህ በተጨማሪ በካልፎርኒያ፣ በአይስላንድ፣ ስፔን እና ጋና የተነሱ የምድር ፎቶዎች የየዘርፉ አሸናፊ መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
የምድር ፎቶ ውድድር እ.ኤ.አ ከ1480ዎቹ አንስቶ መካሄድ የጀመረ ሲሆን የዘንድሮው አሸናፊዎች በለንደን ከሮያል የጂኦግራፊ ማህበረሰብ ሽልማታቸውን የሚቀበሉ ይሆናል ተብሏል።