የኢትዮጵያ ዲያስፖራ የሠላም ጓድ በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ሠጡ


ነሃሴ 04/2013 (ዋልታ) –
የኢትዮጵያ ዲያስፖራ የሠላም ጓድ በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ እና የዲያስፖራው ሚናን በተመለከተ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ተገኝተው መግለጫ ሠጡ ::
የሰላም ልዑኩ ወደ ኢትዮጵያ ከገቡ ሦስት ሳምንት የሆናቸው ሲሆን ከአስራ ሶስት የሲቪክ ማህበራት መምጣታቸውን አስታውቀዋል ::
ልዑኩ ዘጠኝ አባላትን ይዞ ነው ወደ ኢትዮጵያ የገባው ::
የኢትዮጰያ መንግስት እየወሰደ በሚገኘው የህግ ማስከበር እርምጃ ዲያስፖራው በሚኖው ሚና ዙሪያ የሰላም ልዑኩ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር መወያየታቸውን የኢትዮጰያ ዲያስፖራ የሰላም ጓድ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር ብሩክ ሀይሉ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል::
በተለይም የሰለም ልዑኩ በአሁን ሰአት የተቃጣብንን ሀገር የማፍረስ አጀንዳ ከኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት በጋራ ለመመከት ዝግጁ ነን ነው ያሉት::
የሰላም ልዑኩ በውጭ የሚገኙ ዲያስፖራዎች በሀገር ጉዳይ በጋራ እና በአንድ ድምፅ መቆም እንዲችሉ ለማድረግ እየስራ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዘር እና በጐጥ የተከፋፈሉትንም በሀገር ጉዳይ ላይ እንዳይከፋፈሉ ለማድረግ ትልቅ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል::
በተለያዩ ቦታዎ ባጋጠመ የሠላም መደፍረስ ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖችን በተለይም በተለያዩ ቦታዎች በመጠለያ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ልኡኩ መጐብኘቱን እና ድጋፍ ማድረጉን ገልፀዋል::
ልዑኩ ሲመለስም ለዲያስፖራው አባላት እና ለተቀረው የአለም ህዝብ በኢትዮጵያ ያለውን እውነታ ለማስረዳት ጥረት እናደርጋለን ብለዋል::
(በሜሮን መስፍን)