ባሳለፍነው ታህሳስ ወር ብቻ ከ 344 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የተለያዩ የገቢ እና ወጪ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በዚህም ግምታዊ ዋጋቸው ብር 274ሚሊየን 708 ሺህ 289 የሆኑ የገቢ ኮንትሮባንድ ዕቃዎችና ህገወጥ ገንዘቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
በሌላ በኩል ከ 70 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የተለያዩ ወጪ የኮንትሮባንድ አይነቶች መያዛቸውን በታህሳስ ወር የኮንትሮባንድ መካከል ስራዎች ሪፖርት ተመላክቷል፡፡
በአጠቃላይ 344 ሚሊየን 715 ሺህ 978 በር የሚያወጡ ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተይዘዋል፡፡
በገቢ ኮንትሮባንድ የተያዙት ዕቃዎች በተለይም በጅጅጋ፣ በሀዋሳ፣ በድሬዳዋ፣ በሞያሌና ኮምቦልቻ ቀዳሚውዎቹን ስፍራዎች ሲይዙ፤ በወጪ ኮንትሮባንድ አዲስ አበባ ፣ ሃዋሳ፣ ሞያሌ፣ ጅማ እና ጅጅጋ ከፍተኛ መጠን ያለው የኮንትሮባንድ ዕቃ የተያዙ መሆኑ ተገልጿል፡፡
አደንዛዥ ዕፆች፣ ህገወጥ ገንዘብ፣ የተለያዩ የግብርና ምርቶች፣ ማዕድናት እና የቁም እንስሳት ሲሆኑ በገቢ ኮንትሮባንድ ደግሞ ልባሽ ጨርቆች፣ ኤሌክትሮኒክሶች፣ የምግብ ምርቶች፣ የጦር መሳሪያዎች፣ መድኃኒትና ሌሎችም ዕቃዎች መያዛቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡