ግንቦት 11/2013(ዋልታ) – የህዳሴው ግድብ አጠቃላይ የግንባታ ሂደት 80 በመቶ በላይ መድረሱን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ አስተባባሪ ምክር ቤት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በህዳሴው ግድብ የግንባታ ሂደት ላይ ከሃይማኖት ተቋማት ጉባኤና ከሲቪክ ማህበራት ጋር የምክክር መድረክ እያካሄደ መሆኑ ታውቋል።