የህዳሴ ግድብ በተያዘው የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ

መስከረም 30/2015 (ዋልታ) በአዲሱ በጀት ዓመት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በተያዘው የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ በትኩረት እንደሚሰራ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ፡፡

በበጀት ዓመቱ በባለፈው በጀት ዓመት የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች በመለየት በኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚሰራም ፕሬዝዳንቷ በ6ኛው ዙር የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች እና ፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል።

መንግስት የሰሜኑን ጦርነት በሰላም ለመቋጨት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራም በንግግራቸው አመልክተዋል።

በፍትህ ሥርዓቱ ላይ ቀልጣፋ አገልግሎት ለተገልጋዩ ማህበረሰብ ለመስጠት መስራት የአዲሱ ዓመት የትኩረት አቅጣጫ እንደሆነም ገልፀዋል።

የቱሪዝም ዘርፉን ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ በትኩረት እንደሚሰራ የገለፁት ፕሬዝዳንቷ የወደሙ መሰረተ ልማቶችን ዳግም መልሶ የመገንባት ስራ እንደሚከናወንም ነው የጠቆሙት።

በ2015 በጀት ዓመት ውይይቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም ነው ፕሬዝዳንቷ የገለፁት።

በሱራፌል መንግስቴ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!