2014 ዓ.ም መንግስት የሰሜኑ ጦርነት በሰላም እንዲቋጭ በርካታ ጥረቶች ያደረገበት ዓመት እንደሆነ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

መስከረም 30/2015 (ዋልታ) 2014 ዓ.ም መንግስት የሰሜኑ ጦርነት በሰላም እንዲቋጭ በርካታ ጥረቶች ያደረገበት ዓመት እንደሆነ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ

6ኛው ዙር የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች እና ፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ይገኛል።

በምክር ቤቶቹ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ያገባደድነው 2014 ዓ.ም ህዝቡ የሚፈልገውን መንግስት በመምረጥ ነፃና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ያካሄደበት ዓመት እንደሆነ ገልጸዋል።

መንግስት የሰሜኑ ጦርነት በሰላም እንዲቋጭ በርካታ ጥረቶች ያደረገበት ዓመት እንደሆነም አመላክተዋል፡፡

በ2014 ዓ.ም በርካታ ጫናዎች ቢከሰቱም በኢኮኖሚ ላይ ስኬት መመዝገቡን ያነሱት ፕሬዝዳንቷ ባለፉት ተከታታይ ዓመታት የውጪ ምንዛሬ እድገት ማሳየቱንም ጠቁመዋል።

እንደማሳያም በኤክስፖርት ዘርፍ የታየው ውጤት ከፍተኛ መሆኑንም ነው ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የተናገሩት።

መንግስት በ2014 በጀት ለ2 ነጥብ 38 ሚሊዮን ዜጎች የስራ እድል እንደፈጠረም ጠቁመዋል።

የተመዘገቡ አዎንታዊ ውጤቶች እንዳሉ ሁሉ በበጀት ዓመት የተከሰተው የኑሮ ውድነት በአሉታዊ ጎን የሚነሳ ነውም ብለዋል።

የኑሮ ውድነትም ለመቀነስ በዘንድሮ ዓመት በትኩረት ይሰራል ብለዋል ፕሬዝዳንቷ።

በሱራፌል መንግስቴ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!