የምክር ቤቱ የሴቶች ኮከስ አባላት ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ

ነሐሴ 13/2013 (ዋልታ) – የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶች ኮከስ አባላት ለመከላከያ ሰራዊት የስንቅ ድጋፍ አደረጉ።
የስንቅ ድጋፋ በሶ፣ ቆሎ፣ ኮቾሮ እንዲሁም ብርድ ልብስን ጨምሮ የሴቶች የንጽሕና መጠበቂያ ሞዴሶችን ያካተተ ነው ተብሏል።
በአጠቃላይ ድጋፋ በገንዘብ ሲተመን 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር እንደሚገመት ተገልጿል።
ድጋፋን የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሽታዬ ምናለ፣ የምክር ቤቱ የሴቶች ኮከስ ሰብሳቢ ወይዘሮ አበባዬ ገዛኸኝ ለመከላከያ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ማርታ ሉጂ አስረክበዋል።
የምክር ቤቱ አባላት ከዚህ ቀደም ለመከላከያ ሰራዊት የአንድ ወር ደመወዛቸውን በአጠቃላይ 7 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር የሰጡ ሲሆን፤ የደም ልገሳ ማካሄዳቸውንም ኢዜአ ዘግቧል።