ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ አንካራ የነበራቸው ቆይታ ውጤታማ ነበር – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ነሐሴ 13/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በፖለቲካ እና በዲፕሎማሲው ረገድ በቱርክ አንካራ የነበራቸው ቆይታ ውጤታማ እና የተሰካ እንደነበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት ስምንታዊ መግለጫ አረጋግጠዋል::
ቱርክ እና ኢትዮጵያ መከላከያ ሀይል እና በውሀ ልማት ዘርፍ ስምምነት መፈራረማቸውን አስታውቀዋል ::
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጀፍሪ ፊልትማን ጋር ተገናኘተው በኢትዮጰያ እና በአሜሪካ ግንኙነት ዙሪያ መክረዋል ብለዋል አምባሳደሩ።
በተለይም ኢትዮጵያ እያካሄደች ስላለው ህግ የማስከበር እርምጃ ከጅምሩ አንስተው ለልዩ መልዕክተኛው ማስረዳታቸውን ገልጸዋል ::
የህወሓት የሽብር ቡድን በማይካድራ እና በአፋር የፈፀመውን ዘግናኛ ጭፍጨፋ አሜሪካ ለምን በቸልተኛነት አለፈችው በማለት በግልፅ ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን ጄፍሪ ፊልትማን በበኩላቸው አሜሪካ የኢትዮጵያ ሉአላዊነት እንዲጠበቅ ትስራለች ያሉ ሲሆን አሁን ያለው ግጭት በሰላም እንዲፈታ በማሰብ ብቻ ነው አሁን እያደረግን ያለው እንቅስቃሴ ብለዋል ::
በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች አምባሳደሮች ለአብነት የደቡብ ሱዳን ፣ የሴኔጋል ፣ የባህሬን እና የሳውዲ በኢትዮጰያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ እውነታውን ለሀገሪቱ መረጃ መስጠታቸው ተገልጸዋል፡፡
በተለይም በሳውዲ የኢትዮጵያ አምባሳደር በሳውዲ ስላሉ ኢትዮጵያውያኖች ወቅታዊ ሁኔታ ጠንከር ያለ ውይይት ከሃገሪቱ መንግስት ጋር ማድረጋቸው ታውቋል::
በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎች በተለየ መልኩ ለሀገራቸው ድጋፍ ማድጋቸው ነው የተገለፀው ::
በተለይም በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን ያልተገባ ጫና በመቃወም ሰልፉ በማድረግ እና ለተፈናቀሉ ኢትዮጵያዊያን አፋጣኘ ድጋፍ በማድረግ ለሀገራቸው ትልቅ ስራ መስራታቸውን ነው አምባሳደር ዲና ያስታወቁት ::
በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲም በዚህ ሳምንት ከጅቡቲ 49፣ ከሱዳን 60፣ ከየመን 79 ዜጐችን ወደ ሀገር ለመመለስ መቻሉ ነው የተገለጸው ::
(በሜሮን መስፍን)