የሰላም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር በሰብዓዊ መብት አጠባበቅ ዙሪያ ተወያየ

የሰላም ሚኒስቴር

ሚያዝያ 15/2013 (ዋልታ) – የሰላም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጋር በሰብዓዊ መብት አጠባበቅ ዙሪያ ተወያየ፡፡

የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ ጋር የሰብዓዊ መብት አጠባበቅ እንዲሁም ቀጣይ የትብብር መስኮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።