የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ 12 ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ጉዞ ጀመሩ

የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች

ኅዳር 9/2015 (ዋልታ) በዓለም ምግብ ፕሮግራም አስተባባሪነት የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ 12 ተሽከርካሪዎች በዛሬው ዕለት በአፋር ክልል በኩል ወደ ትግራይ ክልል ጉዞ መጀመራቸው ተገለጸ፡፡

የዓለም የምግብ ፕሮግራም በአፋር ክልል በኩል ለትግራይ ክልል ህዝብ የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ እያደረገ እንደሚገኝ ነው የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመላከተው፡፡

በዚህም ሁለት የነዳጅ ቦቴዎችን ጨምሮ የሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ 12 ተሽከርካሪዎች ዛሬ በአፋር ኮሪደር በኩል ወደ ትግራይ ክልል ጉዞ ጀምረዋል፡፡

የአፋር ሕዝብና መንግስት ለወንድም የትግራይ ሕዝብ የሰብዓዊ እርዳታው እንዲደርስ ካሁን በፊት ሲያደርገው እንደነበረው ሁሉ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሠራም መረጃው አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW