የአፋር ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ ነገ ይጀመራል

ሰኔ 18/2013 (ዋልታ) – የአፋር  ክልል ምክር ቤት  ሶስተኛው  አስቸኳይ ጉባኤ  ነገ በሰመራ ከተማ  እንደሚጀመር  የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ  አስታወቁ።

የምክር ቤቱ ዋና አፈ-ጉባኤ አሚና ሴኮ ለኢዜአ እንደገለጹት፣  የክልሉ ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ ስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላምና በስኬት በተጠናቀቀበት  ማግስት የሚካሄድ መሆኑ ልዩ ያደርገዋል።

በምርጫው  የድምጽ አሰጣጥ ሂደት በስኬት  እንዲጠናቀቅ ቁልፍ ሚና ለተጫወቱ በዋናነት ህብረተሰቡ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የጸጥታ መዋቅሩ የክልሉ ምክር ቤት አክብሮቱ ከፍተኛ መሆኑን አስታውቀዋል።

በተጨማሪም የተለያዩ የአስፈጻሚ አካላትን ተግባርና ሃላፊነት ለመደንገግ የወጡ  አዋጆችም ለምክር ቤቱ ቀርበው ውይይት ከተደረገበት በኋላ  እንደሚጸድቅ ይጠበቃል።

የአፋር ክልል ምክር ቤት 96 አባላት ያሉትና  አስቸኳይ  ጉባኤውም  የምክር ቤቱ የስራ ዘመን ማጠናቀቂያ እንደሚሆንም ተመልክቷል።