የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማህመት በታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ

ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ

መጋቢት 09/2013 (ዋልታ) – የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማህመት በታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ማጉፉሊ ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ፡፡

ሊቀመንበሩ አህጉሪቷ ቁርጠኛ የፓን አፍሪካኒስት መሪ አጥታለች ሲሉ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

በተጨማሪም በምስራቅ አፍሪካ ባለው ቀጠናዊ ትብብር ትልቅ ድርሻ እንደነበራቸውም ነው ያስታወሱት፡፡

ሊቀመንበሩ ለታንዛኒያ ሕዝብና መንግስት መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

ጆን ማጉፉሊ ሌሊቱን ለህልፈት መዳረጋቸውን የሃገሪቱ ምክትል ፕሬዚዳንት መግለጻቸው ይታወሳል፡፡