የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባ በዛሬው ዕለት እንደሚጠናቀቅ አስታወቀ

ግንቦት 06/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመላው ሀገሪቱ በ11 ክልሎች እና ሁለት ከተማ መስተዳድሮች ሲካሄድ የቆየው የመራጮች ምዝገባ ዛሬ እንደሚጠናቀቅ አስታወቀ።
በዚህም በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር፣ በአፋር ክልል፣በአማራ ክልል፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ በድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር፣ በሃረሪ ክልል፣ በኦሮሚያ ክልል፣ በጋምቤላ ክልል፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል፣ በሲዳማ ክልል እንዲሁም ሶማሌ ክልል የድምጽ መስጫ ካርድ የመውሰጃ የመጨረሻ ቀን ዛሬ በመሆኑ የድምጽ መስጫ ካርድ ያልወሰዱ ዜጎች እንድወስዱ ቡዱ ጥሪ አቅርቧል።
ለዜጎች መረጃ የሚያቀርቡ ሚዲያዎች፣ ማህበራዊ ሚዲያ ተሳታፊዎች እና የፖለቲካ ፓርቲዎች እጩዎች የምዝገባ የመጨረሻው ቀን ዛሬ መሆኑን በማስታወስ ዜጎች ካርዳቸውን እንዲወስዱ እንዲያበረታቱም ማሳሰቡን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡