የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳን አስመልክቶ የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው

Image may contain: 1 person, sitting

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የምርጫ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳን አስመልክቶ የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው።

መጪውን 6ኛው አገራዊ ምርጫን አስመልክቶ ከሲቪል ማህበራት፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎችና ከሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር ምክክር ሲያደርግ የነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመጣውን ውጤት ለዛሬው መድረክ ያቀርባል።

ምርጫው ሊከናወን የሚችልባቸውን ቀናት ተግባራትና ሁኔታዎችን አስመልክቶ ምክክሮችን ሲያደርግ የቆየው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፤ ከዚህ ቀደም ከተከናወኑ ምክክሮች በኋላ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ያስተዋውቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የምርጫ ጊዜያዊ የጊዜ ሰሌዳ ይፋ በማድረግም በጊዜ ሰሌዳው ላይ ያሉ ቀዳሚ ተግባራትን አስመልክቶ ቦርዱ መረጃ እንደሚሰጥ ኢዜአ ዘግቧል፡፡