የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እያሻቀበ በመምጣቱ ህረተሰቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባው ቢሮው አሳሰበ

ሚያዚያ 08/2013 (ዋልታ) –  የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ዛሬ በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው በኦሮሚያ ክልል 32ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከ370 በላይ ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉንና ህይወታቸው ከሚያልፉ ሰዎች መካከል 12 በመቶ የሚሆኑት ወጣቶች መሆናቸውን አስታውቋል፡፡

በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከማሻቀቡ በተጨማሪ ከወትሮው ጊዜ በተለየ በፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ ሰዎች ለበርካታ ቀናት መቆየታቸው ሁኔታውን በእጅጉ አሳሳቢ አድርጎታል ሲል በመግለጫው አስታውቋል፡፡

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መንግስቱ በመግለጫው ላይ እንዳነሱት የቫይረሱ ምልክቶች ከተለመደው ውጪ ባህሪን እያሳዩ በመሆናቸውና ዜጎች ወደ ጤና ጣቢያ ዘግይተው በመምጣታቸው በርካታ ሰዎች ህይዎታቸው ሊያልፍ ችሏል ብለዋል፡፡
ህብረተሰቡ ለቫይረሱ ያለው ግንዛቤ ዝቅተኛ መሆኑን ያነሱት ዶ/ር መንግስቱ 40 በመቶ የሚሆኑ የክልሉ ነዋሪዎች የኮሮና ቫይረስ የለም ብለው የሚምኑ መሆኑን ባደረጉት ጥናት ማረጋገጣቸውን አንስተዋል፡፡

እየተባባሰ የመጣው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመግታት የተለያዩ መመሪያዎች መደንገጋቸውን የገለፁት የኦሮሚያ ጠቅላይ ዐቃቢ ህግ አቶ ሁሴን እስማኤል ህብረተሰቡ የተደነገጉ መመርያዎችን አውቆ ተፈፃሚ እንዲያደርግ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
እየተባባሰ የመጣውን የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ህዝባዊ ስብሰባዎችን መቀነስና መጪው በዓላት ጥንቃቄ የታከለባቸው መሆን እንደሚገባቸው የክልሉ የጡና ቢሮ ኃላፊ አስታውቀዋል፡፡
(በዙፋን አምባቸው)
<img class=”j1lvzwm4″ src=”data:;base64, ” width=”18″ height=”18″ />
<img class=”j1lvzwm4″ src=”data:;base64, ” width=”18″ height=”18″ />