የዘንድሮው የዓለም የጽዳት ቀን በቦንጋ ከተማ ይከበራል

መስከረም 3/2015 (ዋልታ) ዩኤን ሀቢታት የተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት መስከረም 7 ቀን 2015 ዓ.ም የሚከበረውን የዓለም የጽዳት ቀን አስመልክቶ በቦንጋ ከተማ በዓሉን እንደሚያከብር አሳውቋል፡፡

ድርጅቱ ከዚህ ቀደም በሌሎች የሀገራችን ከተሞች ይህን በዓል ያከበረ ሲሆን የዘንድሮውን የጽዳት ቀን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቦንጋ ከተማ እንደሚያከብር የከተማው ማዘጋጃ ቤት ገልጿል፡፡

በዚህ በዓል ላይ የከተማው ፐብሊክ ሰርቫንቶችን ጨምሮ መላው የከተማው ነዋሪች የሚሳተፉ ሲሆን ድርጅቱ ለጽዳት የሚያገለግሉ የተለያዩ ቁሳቁሶችን፣ እንዲሁም የድርጅቱ አርማ ያለበት አንፀባራቂና ትሸርቶችን ይዞ እንደሚመጣ መገለጹን የከተማው መንግስት ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ጠቁሟል፡፡