የሎጅስቲክ ስርዓቱን በማሻሻል የኢኮኖሚውን ዕድገት ያፋጥናል የተባለለት የደወሌ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎች ተርሚናል ተመረቀ።
ተርሚናሉ የአሽከርካሪዎችን ድካም እንደሚቀንስና ለአካባቢው ነዋሪ የስራ ዕድል እንደሚፈጥር ተጠቁሟል።
የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት፣ ተርሚናሉ ጅቡቲ ድንበር አካባቢ የሚገኝ በመሆኑ ለሚገቡና ለሚወጡ አሽከርካሪዎች የኮቪድ-19 ምርመራና ማቆያ ይሆናል፣ የአሽከር በአካባቢው ለሚገኙ ነዋሪዎች የስራ ዕድል ይፈጥራል፣ በርካታ ከባድ መኪኖችን ይይዛል።
ተርሚናሉ 9 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን፣ እስከ 500 መኪኖች በአንድ ጊዜ መያዝ ይችላል ተብሏል።
ተርሚናሉ 71 ሚሊየን ብር ወጭ ሆኖበት እየተሰራ ሲሆን፣ እስካሁን አጥርና መኪና ማቆሚያ በምዕራፍ አንድ የተሰሩ ናቸው። ምዕራፍ 2 የግንባታ ስራው ይቀጥላል ነው የተባለው።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የሶማሌ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድርና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል።
(በተስፋዬ አባተ)