ሰኔ 04/2013 (ዋልታ) – የፒኮክ መናፈሻ አዲስ ዙ ፓርክ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማዋ ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ ከመከላከያ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ጌታቸዉ ኃይለማርያም፣ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ከፍተኛ አመራሮች፣ ባለድርሻ አካላትና የአካባቢዉ ነዋሪዎች በተገኙበት ተመርቆ በይፋ ስራ ጀምሯል።
ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ የማዕከሉ በዚህ ደረጃ ከፍ ባለ የስነ ምህዳር እና የመካነ እንሰሳት ማዕከልነት ደረጃ መገንባቱ ከተማዋን የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ይዘን የተነሳው አንዱ ውጥን ማሳያ ጅማሮ ነው ብለዋል።
የከተማ አስተዳደሩ በቀጣይም ለማዕከሉ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በማዕከሉ ግንባታ ወቅት ተሳታፊ ለነበሩ አካላት በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በባለ ጥቁር ጎፈር አንበሳ፣ ጭላዳ ዝንጀሮ፣ ሚዳቋና ሌሎች ከ12 በላይ የተለያዩ ዝርያ ያላቸው ከ53 በላይ እንሰሳት በፓርኩ ይገኛሉ።
የፒኮክ መናፈሻ አዲስ ዙ ፓርክ የመከላከያ ሚኒስትር የኮንስትራክሽን አማካኝነት የተገነባ መሆኑን ከከተማ አስተዳደሩ ፕረስ ሴክረተሪ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።